ቤኒን ከ30 ዓመታት በኋላ ነዳጅ ወደ ውጭ መላክ ጀመረች
የምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር 330 ሺህ በርሜል ገደማ የሚሆን የመጀመሪያውን የነዳጅ ጭነት ወደ አውሮፓ መላኳ ተዘግቧል።
ነዳጁ የተገኘው ከ1990ዎቹ መጨረሻ ጀምሮ ሥራ አቁሞ ከነበረው የሴሜ የባሕር ነዳጅ ማውጫ ሥፍራ ነው።
ክሪቲ ጄድ የተባለችው ነዳጅ ጫኝ መርከብ ጭነቱን ከቤኒን የባሕር ዳርቻ መጫኗ የተዘገበ ሲሆን ኅዳር 9 ኔዘርላንድስ፣ ሮተርዳም ትደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል።
👉 የሴሜ የነዳጅ ማውጫ የሚተዳደረውእ.ኤ.አ በ2025 የቁፋሮ ዘመቻ በጀመረው አክራኬ ፔትሮሊየም ኤስ.ኤ ኩባንያ ነው።
#afromekina
Loading content...
