ቻይና የኤሌክትሪክ አውሮፕላን በተሳካ ሁኔታ አበረረች
ቻይና የሰራችው "CE-25A" የተሰኘ የኤሌክትሪክ አውሮፕላን የመጀመሪያውን የሙከራ በረራ በስኬት አጠናቀቀ።
በቻይና የንግድ አውሮፕላን ኮርፖሬሽን (COMAC) እና በታዋቂው የባትሪ አምራች ኩባንያ (CATL) ትብብር የተሰራው ይህ አውሮፕላን፣ በሙከራው ወቅት ሁለት አብራሪዎችንና አንድ መሐንዲስ ይዞ ለ16 ደቂቃዎች ያህል በአየር ላይ ቆይቷል።
19 መንገደኞችን የመያዝ አቅም ያለው ይህ አውሮፕላን፣ ለአጭር ርቀት የከተማ ለከተማ ጉዞዎች ታስቦ የተዘጋጀ ነው።
በአንድ ጊዜ የባትሪ ሙሌት ብቻ እስከ 400 ኪሎ ሜትር መብረር የሚችል ሲሆን፣ ከዚህ ቀደምም 19 ጊዜ ያለ አብራሪ የተደረጉ የሙከራ በረራዎችን በስኬት አልፏል።
በአሁኑ ወቅት አውሮፕላኑ መንገደኞችን በመደበኛነት ማጓጓዝ እንዲጀምር የመንግስት ፈቃድ እየተጠባበቀ ይገኛል።
#afromekina
Loading content...
