ተቋርጦ የቆየው የነዳጅ አቅርቦት ወደ ትግራይ መግባት ጀመረ‼️
ከአንድ ዓመት በላይ ተቋርጦ የቆየው የነዳጅ አቅርቦት ወደ ትግራይ መግባት መጀመሩ ተገለጸ። ነዳጅ በመቐለ በሁለት ማደያዎች በመደበኛነት መከፋፈል መጀመሩ ተመላክቷል።
የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር የኢኮኖሚ ጉዳዮች አስፈጻሚ ቴድሮስ አረጋይ (ዶ/ር) የነዳጅ ዕደላው በቀጣይ በሌሎች ማደያዎችና ወደ ሁሉም የትግራይ አካባቢዎች በተከታታይ እንደሚዳረስ ገልጸዋል።
የነዳጅ ማደያ ባለቤቶች በበኩላቸው ፥ ከአንድ ዓመት በላይ ነዳጅ ወደ ትግራይ ባለመግባቱ በእነርሱም ሆነ እንደ ትግራይ ከፍተኛ ችግር ሲያጋጥም መቆየቱን ጠቅሰው ፤ ይህ ጅማሮ ቀጣይነት ያለውና የሕዝቡን ፍላጎት የሚያሟላ እንዲሆን ጥሪ አቅርበዋል።
የፀጥታ አካላት ደግሞ " በነዳጅ ክፍፍሉ ሂደት ፍትሐዊነት እንዲኖር እንሰራለን " ማለታቸውን የትግራይ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
የነዳጅ አቅርቦት መጀመሩ፣ በነዳጅ መጥፋት ምክንያት ተሰቅሎ የቀረው የትራንስፖርት ታሪፍ ወደ ቀድሞው ዋጋ ተመልሶ የሕዝቡን ኑሮ በማቃለል የነዳጅ መግባቱ ትርጉም ሊሰጥ ይገባል። እንዲሁም ደግሞ ነዳጁ በጥቁር ገበያ እየተቸበቸበ ፤ የጥቂቶችን ኪስ እንዳያደልብና ሕዝቡም እንዳይበዘበዝ ቁጥጥር ሊደረግ ይገባል።
#afromekina
Loading content...
